Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Worku Molla – Gonder Sanki New Music Video!

$
0
0

Sanki Video Clip ሳንኪ / Sanki

 

በሰሜን ጎንደር አርማጭሆ በማሰሮ ደንብ አካባቢ የሚገኝ የቦታ መጠሪያ ሲሆን በዚህ ቀበሌ አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰብ ተወዳጅ ልዩ የባህላዊ ጭፈራ ወይም ዉዝዋዜ አይነት ሳንኪ በመባል ይጠራል፡፡ በመሆኑም የጭፈራዉ ስልት ስያሜ የመጣዉ ከአካባቢዉ መጠሪያ ስም ነዉ፡፡ሳንኪ በዚህ አካባቢ ተጀምሮ በአርማጭሆ በጠገዴና በጭልጋ ቆላማ አካባቢዎች ተዘውትሮ የሚጨፈር የእስክስታ/የጭፈራ/አይነት ነው።አጨፋፈሩ ወይም ስልተ ምቱ በጎንደር የአጨፋፈር አይነት ሆኖ ሪትሙ እጅግ መሳጭ በሆነ ምት ይጨፈርበታል።ይህም ተወዛዋዡ እግሩን ከስር ግጥም አድርጎ ትንሽ ጎንበስ በማለት ሁለቱን እጆቹን ወደ ጉልበቱ አቅጣጫ ጉልበቱን ሳያስነካ ውጥር በማድረግ አውራ ጣቱን በማጣመር እስክስታው በሚደራበት ሰአት ወገቡን እጥፍ ዝርጋ እያደረገ አንገቱን ቀና አድርጎ ማራኪ በሆነ አጨፋፈር የሚጨፍረው የአጨፋፈር አይነት ነው። ድምፃዊ ወርቁ ሞላ ይህን ባህላዊ የጎንደር ጭፈራ ስልት ከቦታዉ ሳንኪ እና ላይአርማጭሆ ድረስ በመሄድ እንዲህ በአማረ መልኩ በዚያ በሚያምር መልክአ-ምድር ቀረጻዉን በማከናወን ለወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ አበርክቷል፡፡ ወርቅሻ እናመሰግናለን ፤ እግዚአብሄር ይባርክህ፤በርታልን እንዲህ የማይታወቁ አዳዲስ ባህላዊ ዉዝዋዜዎችን ወደፊት እንደምታሳዉቀን ተስፋ እናደርጋለን፡፡በዉዝዋዜዉ ላይ የተሳተፋችሁ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን በጣም እናመሰግናለን፤በርቱ ፤ኮርተንባችኃል እናተ አዲሱ ትዉልድ የጎንደር ባህላዊ ሙዚቃ ዉዝዋዜ አምባሳደሮች ናችሁ፡፡

ምንጭ:-አሹ ዋሴ ከጎንደር


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles