Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

George Weah sworn in as President of Liberia

$
0
0

አዲሱ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊሃ ቃለ መሃላ ፈጸሙ።

በመዲናዋ ሞኖሮቪያ በሚገኘው ሳሙኤል ዶይ ስታዲየም በተካሄደው ቃለ መሃላ የመፈጸም ስነ ስርዓት በርካታ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንቱ የህዝባቸውን ፍላጎት ለማሟላት የተቻላቸውን እንደሚያደርጉ በስነ ስርዓቱ ወቅት ለተሰበሰበው ህዝብ ተናግረዋል።

የተሻለውን ለማድረግ እንዘጋጅ ሲሉም በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

ሃገሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግም እጅ ለእጅ ተያይዘን ጠንካራ ስራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል በመልዕክታቸው።

የህዝቡን ፍላጎትም ሆነ ሌሎች ለውጦች እንዲሳኩ ግን ላይቤሪያውያን የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በሃገሪቱ ያለውን ሙስና ማስወገድና የተዳከመውን የሃገሪቱን ኢኮኖሚ በማነቃቃት የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የፕሬዚዳንቱ ቀጣይ የቤት ስራዎች ይሆናሉ።

በብረት ጥሬ እቃዎችና በጎማ ዛፍ ምርቶች ኢኮኖሚዋ የተንጠለጠለው ላይቤሪያ በርካታ ዜጎቿ ከድህነት ወለል በታች የሚገኙባት ሃገር ናት።

ባለፉት ጊዜያት ተከስቶ የነበረው የኢቦላ ወረርሽኝም የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ እንደጎዳው ይነገራል።

ጆርጅ ዊሃ ባለፈው ታህሳስ ወር በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ 61 ነጥብ 5 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸው ይታወሳል።

The post George Weah sworn in as President of Liberia appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles