Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Living risk to risk’: the new wave of African migrants deported from Israel

$
0
0

ከእስራኤል የተባረሩ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመግባት ሲሉ ህይወታቸውን አደጋ ላይ እየጣሉ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስጠነቀቀ።

እንደኮሚሽኑ ገለፃ ከሆነ ሮም ላይ ካነጋገራቸው 80 ኤርትራዊን መካከል አብዛኛዎቹ የመካከለኛዋ ምሥራቅ ሃገርን ለመልቀቅ ከእስራኤል መንግሥት የሚሰጠውን ገንዘብ ተጠቅመው በሰሜን አፍሪካ በኩል ወደ አውሮፓ አደገኛ የሚባለውን ጉዞ አድርገዋል።

ስደተኞቹ 3500 ዶላር ተሰጥቷቸው ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ወይም ወደተስማሙበት ሶስተኛ ሃገር እንዲሻገሩ ይደረጋል።

ሆኖም አብዛኛዎቹ ወደ ሰሜን በማቅናት በሊቢያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት ሜድትራኒያንን ያቋርጣሉ።

በጉዟቸው ወቅትም ሁሉም መጎሳቆል፣ እንግልትና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው የኮሚሽኑ መግለጫ አመልክቷል።

እስራኤል በዕቅዷ መሠረት አብዛኛዎቹ ከኤርትራ እና ከሱዳን የሆኑትን ከ30 ሺህ በላይ ስደተኞችን አስገድዳ ከሀገር እንዲወጡ የምታደርግ ከሆነ ብዙዎች ህይወታቸውን አደጋ ላይ ሊጥሉ ይችላሉ ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠንቅቋል።

ሁሉም ስደተኞች እስከመጪው ሚያዝያ ድረስ ሃገሪቱን ለቀው የማይወጡ ከሆነ እስር እንደሚጠብቃቸው እስራኤል ባለፈው ሳምንት ገልጻለች።

እስራኤል “ኤርትራዊያንና ሱዳናዊያንን ከሰሃራ በታች ወደሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት የማስፈር ፖሊሲዋን እንድታቆም” ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

ዕቅዱ”ወጥነት” የሌለው እና ግልጽ ያለሆነ ነው ያሉት የተባበሩት መንግሥታት ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ዊሊያም ስፒንድለር፤ እስራኤል ሌላ መፍትሔ እንድታቀርብም ጠይቀዋል

The post Living risk to risk’: the new wave of African migrants deported from Israel appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles