አርቲስት ለማ ጉያ ላለፉት 65 ዓመታት ከ10 ሺህ በላይ ሥዕሎችን በፍየል ቆዳ ላይ በመሳል አድናቆትን አትርፈዋል።
ሥዕሎቻቸውን ከአካባቢያቸው የሚያገኟቸው ተፈጥሯዊ ነገሮች በመጠቀም የሚያዘጋጁ ሲሆን ልጆቻቸውን ጨምሮ አምስት የሥዕል ሙያቸው ተከታዮችን ለማፍራት ችለዋል።
ሥራዎቻቸውንም በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ‘ለማ ጉያ የሥነ-ጥበብ ማዕከል’ ውስጥ ለጎብኝዎች ያሳያሉ።
ለማ ጉያ ይህን ሥዕል ከሠሩት 42 ዓመታት ተቆጥረዋል። የአፍሪካ መሪዎችን በድመቶቹ መስለው የሀገራቸውን ሃብት በሙስና ሲመዘብሩ፣ በአልጋው ሥር የሚታዩት የአህጉሪቷ ጠላት አይጦች ደግሞ የአፍሪካን ሃብት ሲቀራመቱ ይታያሉ፤ እየፈሰሰ ያለው ወተትም ያለጥቅም ለዘመናት የሚፈሱት የአፍሪካ ወንዞች ምሳሌ ነው።

The post Ethiopia: Artist Lemma Guya paintings appeared first on Bawza NewsPaper.