ሰሞኑን ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልሎች ግጭት ጋር ተያይዞ መታወቂያ ላይ ብሔር መስፈሩ አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል። በተለይም መታወቂያ ላይ ያለ የብሔር ማንነት ሰዎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል በሚልም ጉዳዩ መከራከሪያ ሆኗል።
ምንም እንኳን ብሔርን መታወቂያ ላይ መጥቀስ መንግሥት ከዘረጋው ማንነትን መሰረት ካደረገው ፌዴራሊዝም ጋር 26 ዓመታትን ቢያስቆጥርም አሁንም ጥያቄ የሚነሳበት ጉዳይ ሆኗል።
ከሚነሱት አከራካሪ ጉዳዮች ውስጥ ከተለያዩ ብሔሮች የተወለዱ ሰዎች አንድ ብሔር ብቻ እንዲመርጡ መገደዳቸው፤ የብሔር ማንነት አይገልፀንም የሚሉ፤ ብሔር የሚለው ቃል አንድን ማሕበረሰብን አይገልፅም የሚሉት ይገኙበታል። ከዚህ በተቃራኒው ብሔር ማንነትን የሚገልፅ በመሆኑ መታወቂያ ላይ እንዲካተት አጥብቀው የሚከራከሩም አሉ።
ብሔር መታወቂያ ላይ መካተቱን ከሚቃወሙት አንዱ የፊልም ባለሙያ የሆነው ያሬድ ሹመቴ ይህንን ለማስቄር ብዙ እርቀት ተጉዟል። “ብሔር ለሚለው ሀሳብ ለኔ ኢትዮጵያ የምትለው ትበቃኛለች።” በማለትም ይናገራል።
መጀመሪያ መታወቂያውን ሲያወጣ ብዙ ያላሰላሰለበት ያሬድ እንደ ብዙ ኢትዮጵያዊ በቅፅ በተሞላው መስፈርት መሰረት ነው መታወቂያ ያወጣው። ምንም እንኳን መታወቂያው ከወጣ ብዙ ዓመታት ቢያስቆጥርም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ባንክ ቤት ብር ለማውጣት ወይም ለተለያዩ ጉዳዮች መታወቂያውን በሚጠቀምበት ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ ይረበሽው እንደነበር ይናገራል ።
ከዛም ለማምለጥ የሥራ መታወቂያን፣ መንጃ ፍቃድን እንዲሁም ፓስፖርቱን መጠቀም ጀመረ። በተለይም ባለፉት ሁለት ዓመታት ሀገሪቱ ላይ ባለው ብሔርን መሰረት ያደረጉ ግጭትና ውጥረቶች ጋር ተያይዞ የበለጠ መታወቂያው ላይ ብሔር ብሎ መስፈሩን ሊቀበለው አልቻለም። “በብሔር ምክንያት የወዳጆች ግንኙነት እየተበላሸ፤ ለብዙዎች በሰላም ከሚኖሩበት ቦታ ለመፈናቀል ምክንያት በመሆኑ አደገኛነቱ እየጎላ መጥቷል። ” በማለት የሚናገረው ያሬድ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ብሔርን መተው ለሚፈልጉ መነሳሳትን ሊፈጥር እንደሚችል ያስረዳል። BBC amharic
Read more:
The post Ethiopian constitution says nothing about writing ethnicity on identification card. appeared first on Bawza NewsPaper.