Ethiopia:Artist Hachalu Hundessa performing | "ሃጫሉ ሁንዴሳ" እኛ ሞ…
Ethiopia:Artist Hachalu Hundessa performing | "ሃጫሉ ሁንዴሳ" እኛ ሞተን ሌላው አይኖርም እንተላለቃታለን እንጂ…!በአዲስአበባ ሚሊየም አዳራሽ.
Posted by Bawza Ethiopian Newspaper on Saturday, December 9, 2017
እኛ ሞተን ሌላው አይኖርም
እንተላለቃታለን እንጂ
*★★★*
[ ሃጫሉ ሁንዴሳ ]
¶#ኦሮምኛ የማታውቁ ሰዎች #Comment ከመስጠታችሁ በፊት ጦማሩን ብታነቡት ይመረጣል ። ለስድቡ ከዚያ በኋላ ትደረሱበታላችሁ ። ዋናው ጽሑፉ ነው ። ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ግን ዘፈኑን ስሙትና #Comment ስጡ ።
¶ ዛሬ ደግሞ ብዬ ብዬ ጥግብ ስል [ ዘፈን ልጋብዛችሁ ነው ] ግርድፍ ትርጉምም በጽሑፍ መልክ አዘጋጅቼላችኋለሁና አንብቡት። ሁኔታው ግን አስፈሪ ነው ።
#ETHIOPIA | #አዲስአበባ_ሸገር_ፊንፊኔ_አዱገነት ¶ በሚሊየም አዳራሽ ዛሬ ተአምር ታየ ። በአዝማሪ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሽለላ ፣ ቀረርቶና ፉከራ የቴሌቭዥን የቀጥታ ስርጭቱ ተቋረጠ ።
¶ በቴዲ አፍሮ ስንደመም ከቴዲ የባሰ ደፋር በአዲስአበባ ተከስቶ አረፈላችሁ ። የህዝብ ብሶት ምን ጥግ እንደደረሰ ታዩ ዘንድ ይሔን የሃጫሉን ዘፈን አቀረብኩላችሁ ።
¶ ልጁ መዝፈን ብቻ ሳይሆን በዘፈኑ ውስጥ ያስተላለፈው መልእክት በሚገርም ሁኔታ የሆነ በህዝቡ ላይ የቁጭት ፣ የአንድነት ፣ የመበደል ፣ የመረሳት ፣ አሁን ደግሞ ያ በእኛ ዘመን ማብቃት አለበት የሚል ጠንካራ የኦሮሞ ልጆችን አቋም ነው ያስተላለፈው ።
ልጁ ከዚህ በፊት 5 ዓመት በልጅነቱ ታስሮ የተፈታ የአምቦ ልጅ ነው ። ከሳምንት በፊት በጊዮን ሆቴል ኮንሰርት አዘጋጅቶ 2 ሚልየን ብር ቀብድ ከተቀበለ በኋላ የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ኮንሰርቱን ልክ እንደ ቴዲ አፍሮ እንደሰረዘበት ይታወቃል ።
ነገር ግን ዛሬ ” ወገን ለወገን ” በሚል መሪ ቃል በሚሊንየም አዳራሽ ከሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች ማቋቋሚያ የሚውል ገቢ ማሰባሰቢያ በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዶ ነበር ። በዚህ ዝግጅት ላይ እንዲዘፍን የተጋበዘው ደግሞ በኦሮሞ ነገድ ዘንድ ተወዳጅና ተፈቃሪ የሆነው የአምቦ ተወላጁ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አንዱ ነበር ። የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ፣ ዶክተር አብይ አህመድ ፣ አቶ አባዱላ ገመዳ ፣ የህዝብ ግኑኝነቱ አቶ አዲሱ እና በሺህዎች የሚቆጠሩ ታዳምያንም በስፍራው ተገኝተው ነበር ።
በዚህ በሚሊንየም አዳራሽ በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ ግን ማንም ባልጠበቀው ሁኔታ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሰሚንም ተመልካችንም ባስደመመ መልኩ አስደማሚ ድርጊት ፈጽሞ ከህዝብ ፊት መቆም ማለት ምን ማለት እንደሆነ በገሃድ አሳይቷል ።
ወደ ሚዲያ ዘንድ ለኢንተርቪው ሲቀርቡ ” ሀብታችን ህዝብ ነው” ለሚሉት አፈ ቅቤ ሆደ ጩቤ ሆዳም አርቲስቶች የህዝብ ሀብት መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በድፍረትና በተግባር ያሳየ ድርጊት በመፈጸም ህዝቡን በደስታ አሳብዷል ። ባለ ሥልጣናቱንም አስደምሟል ።
የአብዲ ኢሌ የሱማሌ ልዩ ጦር በምስራቅና በደቡብ ኦሮሚያ ጦርነት ከፍቶ የተፈናቀሉትን መልሶ ለማቋቋም የሚውል ገቢ ለማሰባሰብ ነው ተብሎ በተዘጋጀው “ወገን ለወገን” የሙዚቃ ዝግጅት ላይ የታደመውን ህዝብ ዛሬ አርቲስ ሃጫሉ ዛሬ በግልጽ [ ለምን ቤትህ ቁጭ ብለህ ቶሞታለህ? ፈረስህን ያዝና ጦርህን ይዘህ ወደ 4 ኪሎ ገስግስ ] የሚል ግልጽ መልእክት አስተላልፏል ።
የኦሮሚያ መንግሥት መሰል እንደዛሬው ዓይነት የሙዚቃ ዝግጅቶችን በመላው የኦሮሚያ ከተሞች ለማካሄድ መወሰኑ ደግሞ የበለጠ የኦሮሞ ህዝብ የመረዳዳትና ጠላትን በጋራ የመጋፈጥ ባህሉን እንደ አዲስ እንዲያጠናክርና እንዲነሳሳ ያደርገዋል ሲሉ ታዛቢዎች ይናገራሉ ።
በአፋር ሰመራ በተከበረው የብሔር ብሔር ብሔረሰቦች በአል ላይም 3 ክስተቶች ታዳሚዎችን እንዳስደመሙ ነው የተነገረው። የመጀመሪያው የኦሮምያው ፕሬዝዳንት የኦሮሞ ህዝብ ተፈናቅሎ እኔ ነጭ ልብስ አልለብስም ብለው [ ጥቁር የሀዘን ልብስ ] ለብሰው መቅረባቸው ፣ በትርኢቱ ላይ የኦሮሞ ተወካዮች ያለዘፈን በዝምታ በአርምሞ ማሳለፋቸውና በመጨረሻም እብዱ አብዲ ጊሌን ኦሮሞን በማፈናቀሉ ነው በተባለ መልኩ [ የዋንጫ ሽልማት መቀበሉና ከህወሓቱ አይተ ደብረ ጽዮን ጋር በተለየ መልኩ ሲተሻሹ መታየታቸው ነው ።
ለማንኛውም ሃጫሉ ዛሬ እንዲህ ብሎ ነበር የሸለለው ።
አላችሁ? የቦረና ልጆች አላችሁ? የወለጋ ልጆች አላችሁ ? የሐረርጌ ልጆች አላችሁ? የአርሲ ልጆች አላችሁ ? የት ነው ያላችሁት ቦሌ ነው ያለነው በሉ ብሏቸው ነው በሰላምታ የሚጀምረው ።
Geerar geerar naan jettuu
Mee ka’ee itti haleeluuree
Badi badi naan jettuu
Mee ka’ee qajeeluuree
Ani maalan geeraraa
Anoo yaadan yeelalaa
Dhiirri geeraree hin quufne
Hidhaa # qaallitti jiraa
Dhiirri geeraree hin quufne
Hidhaa # qilinxoo jiraa
Dhiirri geeraree hin quufne
Hidhaa # karchallee jiraa
Karchallee # Amboo jiraa
Anoo maalan geeraraa
Anoo yaadan yeelalaa
Yaa ijoollee banneerrakaa
Gurra abbaa ganneerrakaa
Oromoon maalum godheree
Maalum gochuu dideree
Yaalle amma dandeenyu
Kana caala maal goonuuf
Xinnaas gabbarree guddaa
Akka wajjin bubbullu
Obsuun waanuma jiruu
Obsinee amma obsaa
Erga sodaa fakkaate
Ka’een ishitti cabsaa
Nan dhowwinaa nan dhaqaa
Iddoo yartuun nu nyaartee
Amma isheen geessu laalaa
Akka lamuu nu nyaarretti
Biyyeetti ishii dabalaa
Yaa Ijoollee biyya kooti
Hundumtuu haadhoo kooti
Sa’aa keenya ishee burree
ishee ribbiif kennine
Gaadi’aniit elmatu
Elmatan bara meeqa
Nuuf galchuu didan malee
Yoom beekne dubbii Keessaa
Akka ramacii ibiddaa
Irra keessa dibanii
Nu gubuuf akka yaadan
Rabbumaaf jirra malee
Harargeen mancaa qarraan
Tuulamni farda leenjise
Roorroon daangaa dabarraan
Qeerroon falma murteesse
Addaggeen safuu hin beektu
Yaa qeerroo
Addarra dhaaban malee
Falmadhu qeerroo Sii’i
Abdiin sabaa yoomillee
Nu beekuuf bar shororkaa’u
Kanaaf garaa jabaatu
Irreef humna qabaniin
Ijibbaata falmatu
Nuun miti farda keenya
Hin beeku bareechanii
Gaafa gaarreen aduwaa
Gaafa maqalee sanii
.
.
.Kaafadhu farda keen Loli #Araat_kiiloof situ
aane….
#Haceetu Bookkise akkanatti qeerroodhaf!
ትርጉም ! በግርድፉ ።
አንጎራጉር ትሉኛላችሁ ምኑን ላንጎራጉረው ።
ጥፋ ጥፋ ይለኛል ወዴት አባቴ ልጥፋ ።
ዘፍነው ያልጠገቡትን ቂሊንጦ አጉረው
ምኑን ላንጎራጉረው የቱንስ ልዝፈነው
ወጣቱ ወንድሜ አምቦ ከርቸሌ ነው
የትኛውን ብዬ የቱን ላንጎራጉረው
ትላንት የዘፈነው ዛሬ ማዕከላዊ ነው
አረ ወገኖቼ ጠፍተናል…ከዚህ በላይ ምን እናድርግ ፣ አንድላይ ለመኖር ብለን ትንሹንም ትልቁንም ገበርናል ። መታገስ ያለ ነው እስከምንችለው ድረስ ታግሰናል… ነገር ግን መታገሳችን ፍርሃት ከመሰለ ግን ተነስቼ እሰባብራታለሁ ። ተመለስ አትበሉኝ አትከልክሉኝ እሄዳለሁ ሁለተኛ እንዳትተብት ከፈር እቀላቅላታለሁ። የሀገሬ ልጆች ሁሉም የእናቴ ልጅ ነው ። ያቺን ብሬዋን ላማችንን ለርቢ የሰጠናት ዝምብለው ያልቧታል ለእኛ አልመስ ብለውን ፣ በእግዚአብሔር ቸርነት ቆየን ኖርም እንጂ እነሱማ አቃጥለው ለብልበው ሊፈጁን ነበር… ሐረርጌ ሜንጫውን እየሳላ ነው ፣ ቱለማ ፈረሱን እያሰገረ ነው ፣ ሮሮም ድንበሩን ሲያልፍ ቄሮም ትግሉን እያጠነከረ ነው ።
እኛን እኮ ብቻ አይደለም ፈረሶቻችንን ጭምር አሳምረው ያውቋቸዋል ። ያኔ አድዋና የመቀሌ ዘመቻ ላይ የነበሩትን ። ዋሸሁ እንዴ ? ዋሸሁ እንዴ? ዋሻሁ እንዴ ? ዋሸሁ እንዴ እናንት የኦሮሞ ልጆች ።
ኦሮሞ ፈረሶችህን አዘጋጅ ፣ ጦርህን ሳል ፣ ጋቸናህን አዘጋጅ ፣ የከበበህን ጠላት እያየህ ለምን እቤት ተቀምጠህ ቶሞታለህ? ፈረስህን አዘጋጅና በጦርህ ተዋግተህ 4 ኪሎ አጠገብህ ነው ። አምቦ ላይ ጸብ ነው ፣ ሸገር የደረሰ እንደሁ አባት ቢሞት እንኳ ልጅ ስላለ ዘር አይጠፋም ። እኛ ሞተን ሌላው አይኖርም እንተላለቃለን እንጂ እያለ ነው ሃጫሉ ሁንዴሳ በሚሊንየም አዳራሽ ሲቀውጠው የዋለው ። [ በትርጉሜ ስህተት ከተገኘ ለማረም ዝግጁ ነኝ ] ኦሮምኛ ስሜቴ ያዳምጠዋል እንጂ በደንብ ተናጋሪ አይደለሁም ። እናም ከተበላሸ ይቀርታ ይደረግልኝ ።
እናም ይሔ ነገር በዚህ ከቀጠለና የህዝብ ብሶት በአርቲስቶች እየታጀበ በባለሥልጣናት ፊትና በቴሌቭዥን መቅረብ ከጀመረ ሁሉ ነገር እንደ አከተመ ለማወቅ ነብይ መሆንን አይጠይቅም ።
በተለይ #እኛ_ሞተን_ሌላው_በሰላም_አይኖራትም
#ሁላችንም_እንተላለቃለን_እንጂ የምትለዋን ሀረግ በቴሌቭዥን መለቋቋ እየተበደለና እየተፈናቀለና ፣ እየታሰረ ያለውን 50 ሚልዮን ኦሮሞ በቁጭት እንዲነሳ የሚያደርገው ይመስለኛል ። እኔ ግን ሁኔታው አላማረኝም ። በሌላው ገጽም እንዲሁ የሚፎክሩ መኖራቸውን ባሰብኩ ጊዜ ደግሞ አከተመ የሚለውን ደጋግሜ እንዳስብ እያደረገኝ ነው ።
አበቃሁ !
ሻሎም ! ሰላም !
Zemedkun BekeleLike Page
The post Ethiopia:Artist Haacaaluu Hundeessaa performing | “ሃጫሉ ሁንዴሳ” እኛ ሞተን ሌላው አይኖርም እንተላለቃታለን እንጂ…!በአዲስ አበባ በሚሊንየም አዳራሽ. appeared first on Bawza NewsPaper.