የአፕል መስራች ስቲቭ ጆብስ ሲሞት ኩባንያው 700 ቢሊየን ዶላር ይገመት
ነበር ፤ በታሪክ ሀብታሙ ኩባንያ ነበር። ስቲቭ ከመሞቱ ከጥቂት ቀናት በፊት
“ስለ ሕይወት ትርጉም” ትንሽ ማስታወሻ ጥሎልን አልፏል።
ማስታወሻው፦
“በሕይወቴ በቢዝነስ ረገድ የስኬት ጫፍ ላይ ደርሻለሁ ፤ በሌሎች አይን ከኔ
የበለጠ ለስኬት ተምሳሌትነት የሚመረጥ ሰው የለም”
“ነገር ግን ከስራ ባሻገር በሕይወቴ ብዙ ደስታ አልነበረኝም። ሀብታምነት
የተለማመድኩት የህይወቴ አካል ከመሆን ያለፈ ትርጉም አልነበረውም።”
“በዚች ታምሜ አልጋ ላይ በዋልኩበት ቅጽበት ፣ በመላው ሕይወቴ
የተቀበልኩት ሽልማትና ያገኘሁት ሐብት ሞት እየቀረበኝ በመጣ ቁጥር
ትርጉምየለሽ ሆኖብኛል”
“በጨለማው ውስጥ የሕክምና መርጃ መሳሪያዎችን አረንጓዴ መብራት
አያለሁ ፤ ድምፃቸውንም እሰማለሁ። በእያንዳንዷ ሰከንድ የሞት መላእክት
ትንፋሹ እየቀረበኝ ሲመጣ ይሰማኛል”
“አሁን አንድ ነገር ገብቶኛል። በህይወታችን ሙሉ አጥፍተን የማንጨርሰው
ገንዘብ ካገኘን በኋላ ከዚህ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ሌሎች
ዝንባሌዎችን ማዳበር አለብን።”
“ሙዚቃ ፣ ስነጥበብ ወይም መፅሀፍት ሊሆኑ ይችላሉ። የልጅነት ምኞታችንን
መከተል ሌላ ነው ወይም የፍቅር ግንኙነት። መንፈሳዊነትም አለ። ብቻ
ለነፍሳችን የሚሆን ጠቃሚ ግን በገንዘብ ሊገዛ የማይችል ነገር መሆን
አለበት።”
“ገንዘብን ብቻ ማሳደድ ግን በመጨረሻ እንደኔ ጠማማ ፍጥረት አድርጎ
ያስቀራችኋል።”
“እግዚአብሔር ስሜትን የሰጠን ፍቅርን እንድናጣጥም እንጂ ገንዘብ
በሚፈጥርብን የውሸት ስሜት ተታለን እንድንቀር አይደለም”
“ሕይወቴን በሙሉ ካከማቸሁት ግዙፍ ሐብት ውስጥ አንዲት ሳንቲም እንኳን
ይዤ መሄድ አልችልም። ከኔ ጋር ልወስደው የምችለው ብቸኛ ነገር በፍቅር
የቀለሙ ትዝታዎችን ብቻ ነው።”
“ያ ነው እውነተኛ ሃብታችሁ ፣ የማይከዳቹ ወዳጃችሁ። በሄዳችሁበት ሁሉም
ብርሀን እና ጥንካሬ ይሆናችኋል”
“በአለም ላይ ውዱ አልጋ የህመምተኛ አልጋ ነው። አንድ ሰው መኪና
እንዲነዳላችሁ ፣ ስራ እንዲሰራላችሁ ልትቀጥሩ ትችላላችሁ። የናንተን ህመም
ግን ማንም ሊሸከምላችሁ አይችልም።”
“ቁሳዊ ነገሮች ሁሉ ቢጠፉ ሊተኩ ይችላሉ። አንድ ነገር ግን ከጠፋ ዳግም
አይገኝም። እሱም ሕይወት ነው።”
“አሁን በሕይወታችን የትኛውም ደረጃ ላይ ብንሆን መጋረጃው የሚጋረድበት
ቀን ይመጣል።”
“ከወዳጅ ዘመዶቻችሁ ጋር ፍቅርን ተጋሩ”
“እራሳችሁን ተንከባከቡ። ለጓደኞቻችሁ ዋጋ ስጡ”
Chuni First facebook page
The post Steve Jobs | ስቲቭ ከመሞቱ ከጥቂት ቀናት በፊት “ስለ ሕይወት ትርጉም” ትንሽ ማስታወሻ ጥሎልን አልፏል። appeared first on Bawza NewsPaper.