ድሜጥሮስ ዘ”ጎጃም
ንጉስ ካሌብ ከንግስናው በፍቃዱ ቢመንን የገባው ጎጃም ጣና ገዳም ነበር፡፡ቅዱስ ያሬድ ሰነፍ ተማሪ እየተባለ በተወለደበት አካባቢ ቢወቀስ ጎጃም ገብቶ የዜማ ሊቅ ሆነ፡፡ቅዱስ ላሊበላ የገዛ ወንድሞቹ እስከ እየሩሳሌም ቢያሳድዱት ጎጃም ገብቶ በተማረው ጥበብ ሁሉንም አስከነዳቸውና የቅድስና ማዕረግ ተቀዳጅቶ ለዘመናት ምስክር የሚሆኑ ትክል ውቅር ህንፃ ቤተክርስቲያናትን ቆርቁሮልን አልፏል፡፡
ጎዛም፣ጎዣም፣ጎጃም እንደሚሉን ጎጃሞ ማለት አይደለም፡፡ሀይማኖትን ቀድሞ የተቀበለ ህዝብ ማለት ነው፡፡ምክንያቱም በመርጦ ለማርያም ፣በጣና ቂርቆስ እና በፈለገ ግዮን(የአባይ መነሻ)የሀይማኖት የመጀመሪያ፣የቅዱሳን መናሃሪያ፣የትውፊት የስርዓተ ማስፈፀሚያ ሆኖ አገልግሏል፡፡ኢትዮጵያ ከ 6 በላይ የሃይማኖት መፅሐፍትን በዩኒስኮ አስመዝግባለች መፅሐፈ ሔኖክን ጨምሮ ስድስቱም ጎጃም ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ገነት የአባይ ምንጭ ናት፡፡ገነት ጣና ገዳማት ውስጥ ነው የሚሉት የመፅሐፍ ቅዱስ ተመራማሪዎች ለዚህ ይመስላል፡፡(በእርግጥ ገነት እና የህይወት ዛፍ የተሰወሩት ጎጃም እንደሆኑ በሚስጥር የወጣው የቡድን 8 መሪዎች ስብሰባ ጋሀድ ወጥቷል #የሳጥናኤል_ጎል_ኢትዮጵያ በሚልም ታትሟል፡፡ምናልባት ማመን ያለማመን የዚህ ትውልድ ፋንታ ነው፡፡)
ጎጃም ቅድስት ድንግል ማርያምን በጣና ቂርቆስ እና በደብረ ወርቅ ማርያም፣የሙሴ ህግን፣ትዕዛዘ ሰንበትን ቀድሞ ተቀብሏል፡፡በእርግጥም የኤርትራን ባህር የከፈለው እስራኤላዊው ሙሴ ሚስቱ(ሲጳራ ዮቶር)የጎጃም ሰው ነበረች፡፡አማቱም ካህኑ ዮቶር የስልጣን እርከን በማውጣት ሀይማኖትና አገር እንዴት እንደሚመራ ለሙሴ ምክር ለግሶ እንደነበርም ድርሳናት ይመሰክራሉ፡፡
ለዛሬ ከሚቀጥለው ቅኔ በኃላ አበቃሁ—>
“ዘኣምላላኪየ ዘሊ.ኃተግባሩ አዳነ
ለምድረ ጎጃም እቤርት ዘከለንትሃ አባይ
አዲስ ልብስ እንቴሃ ለይሐልቅ በማይ
እምጣነ ዛቲ ትትባረክ ኩሉሔ በቃለ ድርሰት ነብይ”
Tewachew Derso’s post.
The post Demetros | ድሜጥሮስ ! appeared first on Bawza NewsPaper.