ጥቅምት 28/2010ዓም በቤሔራዊ ቲያትር በተመረቀው የፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ “ስውሩና ያልተነገረው የአይሁዳዊያን እና የኢትዮጵያዊያን ታሪክ” የመፅሀፍ ምርቃት ዝግጅት ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የክብር እንግዳ ሆኖ ሲገኝ በአዳራሹ የነበረው ህዝብ ለተመስገን ያሳየው አክብሮት እጅጉን ደስ የሚያሰኝ ነበር።
መድረኩን የሚመራው ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ ይህን ብሏል “በማይናወጥ አቋሙ የሚታወቀው የሁላችንም አንደበት የሆነው በሀገር ውስጥ ከሀገር ወጪ ተቀባይነት ያለው ባለ ብዙው ተከታዩ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በመሀከላችን ይገኛል” ሲል ህዝቡ ከመቀመጫው በመነሳት ለተመስገን ያሳይው ፍቅር ደስ የሚያሰኝ ነበር። በፍቃዱም ንግግሩን ቀጥሎ “ተሜ ለከፈልከው አንዱ ትልቁ ዋጋ እናመሰግናለን” ብሏል ህዝቡም ከተሜ ጋር መሆኑን አሳይቷል።
ተመስገን በወግብና በጀርባ ህመሙ ምክኒያት ብዙ መቀመጥ ሳይችል መፅሀፉን መርቆ ዝግጅቱ ሳያልቅ ለመውጣት ተገዷል።
የመፅሀፍ ምርቃት አዘጋጆችን እና በሔራዊ ቲያትር ቤት የነበሩትን ህዝቦች እጅጉን እናመሰግናለን።
(ቪዲዩን ተመልከቱት)
Tariku Desalegn
Posted by Tariku Desalegn on Friday, November 10, 2017
The post የፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ “ስውሩና ያልተነገረው የአይሁዳዊያን እና የኢትዮጵያዊያን ታሪክ” የመፅሀፍ ምርቃት ዝግጅት ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ.. appeared first on Bawza NewsPaper.