ፈገግታው ተላላ ይመስላል።በፍፁም!ይህ ሰው—አልጋ ወራሹ–በሳውዲ ግዛተ-መንግስት የራሱን ንጉሳዊ ቤተሰብ አይነኬነት ጭምር ጥርሱን በብረት ቦክስ እያነገለ እየቀጣውነው።በተለይ ከሙስና—ማለትም የህዝብ ሀብት ምዝበራ፣ስልጣንን ትራስ አድርጎ ሌሎች ኅላፊዎችን በማስገድድ ራስን መጥቀም፣በፕሮጀክት ስም አየር ለአየር ቅርጥፍ አድርጎ መብላት፣የሀገር ሀብትን ወደ ውጭ መስደድ፣በዘመድ አዝማድ ከቦ-መብላት፣ ጉቦ፣የውለታ-ጉርሻ/kickback/ ስልጣንን ተገን አርጎ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የራስ ለሆኑ ኩባንያዎች የመንግስትን ስራ በቀጥታ መስጠት፣በሰበብ አስባቡ የተለያዩ ግዢዎች እንዲፈፀሙ ወስኖና አስወስኖ ከሻጭ ጋር ተመሳጥሮ በገንዘብ መጥለቅለቅ—ጋር በተያያዘ እንኲን ሊታሰሩና የሆቴል ኮሪደሮች ውስጥ ሊተኙ ቀርቶ ማንም ሱሪ የታጠቀ ወንድ ነኝ ባይ ዝምባቸውን “እሽ!”ሊል አይደፍርም የሚባልላቸውን ኅያል ሰዎች በአንድ ጀምበር ስብስቦ አስሮ ፣የባንክ ሂሳባቸውን አግዶ/ገና ከሳውዲ ውጭ ያላቸውንም ሀብት የማሳገድ መብት አለው/ ሲታይ ይብላኝ ለአፍሪካ የአደባባይ ሌባ ባለስልጣኖች ያሰኛል።ከመሀል የተነሳ የ32 ዓመት አፍላ ጎረምሳ ይህን ማድረግ ከቻለ–በአፍሪካስ–በአዲስ አባስ–በዘረፉት ገንዘብ ካብ ውስጥና በታጠቁት ስልጣን አፈ-ሙዝ ተማምነው እንቅልፋቸውን ለሽ ከማለታቸው የተነሳ –የእነሱ ከፍታ፤የሀገር ግን የመሞቷ ምልክት ሀውልት የሚመስሉ ህንፃዎችን፣ሆቴሎችን፣የገጠገጡ እስከ አሁን የተፈሩ ሙሰኞች-/የውታደራዊ ኅይል አዛዦችን ጨምሮ/ MBS ሊነሳባቸው ይሆን????ስልጣንና ዝርፊያ የተዋለዱበትና ያፈሩት አይነኬነት ቆሌው ተገፈፈ ይሆን?የሀገሪቱን ወጣቶች የለውጥ ጥያቄ የሚያራምድናሰይፉን መዞ ስልጣንና ሙስና ላይ የገነገኑ አሁን በልጣን ላይ ያሉና ልቅቂያለው ብለው “እንግዲህ እፎይ ብዬ የሰረኩትን ልብላ!/ ያሉ ሙሰኞች ጅራፉ ሊጮህባቸው ይሆን?Aፍሪካዊ MBS ከመሀል አድፍጠህ ይሆን?እንጃ—-እንጃ–ኩኩሉ አለ ዶሮ፤ምን ይሰማ ይሆን ጆሮ?/በአንድ ሀገር ፖለቲከኞች በህዝብ ኅላፊነት መንፈስ ተንቀሳቅሰው የሀገርን ችግር ለሁሉም በሚበጅ መልኩ ተነጋግረው እንዳይፈቱ ዋንኛው/የማይታረቅ / እንቅፉት ሙስና ነው።ሙስና ባልተደፈረበት /ግን ለዘመናት ዋልጌ ሆኖ የፈሰሰው አባይ በተደፈረበት ጊዜ/ እንዳሻህ ተብሎ የተለቀቀ ሙስና ፖለቲካውንም፣ኢኮኖሚውንም ጦር ኅይሉንም አገልጋዮቹ እንደሚያደርግ ለማወቅ ምርምር አያሻውም።ሙስና እንደ MBS ያለ ውስጣዊ ጥንካሬ ያለው አፍላ ጎልማሳ–አባ ፈንቅል!–ካልተነሳበት በስተቀር —ይህን እያዘንኩ በተሰበረ ስሜት ነው የምለው—–ሙስና ራሱ ራዕይም ርዕዮት አለምም ይሆናል።ሙስናን ቀንዱን ይዞ መጋጠም የፖለቲካም፣የኢኮኖሚም እንዲሁም ወታደሪያዊ እርምጃ ነው።ሙስና በቁጥጥር ውስጥ በዋለበት ቦታ አገራዊ ጤንነት አለ።
The post ፈገግታው ተላላ ይመስላል።በፍፁም!ይህ ሰው……. appeared first on Bawza NewsPaper.