Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

ለጤዛ ተዋድቀን

$
0
0

“እድሚያችን ሰባ ነው ቢበዛም ሰማንያ”
ይህም ኑሮ ሆኖ ጠዋት ማታ ፍልሚያ

አንዱ ካንዱ ጥዋ: ጥቃት የቀመሰ
በየደጃፉ ላይ ምሽግ እየማሰ
ጦር እንደ ቄጤማ እየነሰነሰ
መንደሩን ሸንሽኖ ባጋም እሾህ ቅጥር
ወገን እያስለየ ባሰለፈን ቁጥር
ጤናችን ሲሸረፍ
ቀናችን ሲዘረፍ
የት ሸሽተን እንትረፍ
የትገብተን እንረፍ?

በዶፍ ዝናብ አገር ለጤዛ ተዋድቀን
ሰላም እንደራበን ደስታ እንደናፈቀን
ትግላችን ሰልፋችን ያከትማል አንድቀን::

(በእውቀቱ ስዩም)

The post ለጤዛ ተዋድቀን appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles