(ለሰለሞን ዴሬሳ ከሱራፌል ወንድሙ)
እንዲህ ነው መነጠል
እንደዚህ ነው ማለፍ
ፀዳል ተጎናፅፎ
አክሊል ተከናንቦ …
እያበሩ መሄድ
እየበሩ መምጣት …
እንዲህ ነው ሳምሳራን
ሰንክሳሩን መስበር
ማለፍ ላለማለፍ
ላለማረፍ ማረፍ
ስለ እውነት መንቃት
በዓለም ላይ መብቃት
ዕውነት፣ ትሁት መሆን
መጠየቅ ማስተንተን …
መፍጠርና ማድነቅ
ቋሚን አለማምለክ …
ገላ ስጋን መጣል
ሰውነትን ማንሳት
የሰው “ዜኒት” ሆኖ ካ’ለም “ናዲር” መራቅ
መጓዝ በጥሞና ፀጥ ብሎ መሳቅ …
ባ’ማዲየስ ሞዛርት፣ በቤቶቨን ፈረስ
በስትራቭንስኪ፣ በባህ በብራህምስ
በሾፐን በሄንድል በቪቫልዲ መፍሰስ …
በጃዝና ብሉዝ በማሪንጌ ቻቻ
በሜሪ በአስናቀች በጂጂ ሙዚቃ
በባቲ ጌሬርሳ ባ’ዝማሪዎች ጭራ
በወለሎ ቅኝት በድቤ ዝየራ …
በእስክንድር በገብሬ፣ በተስፋዬ ስብሃት
ካገርህ ተድረህ አገርህን መፍታት…
ከውቤ በረሃ ትርንጎ ህመሜ
“ታንጎ” ና ፀጋዬ “እቼቼ ገዳሜ”
ከጩታ አዲ’ሳባ፣ ኒው ዮርክና ፓሪስ
እስከ አምባ “ቆራ” ነጭዋ ምኒያፖሊስ …
ሰው ሆነህ ተገልጠህ
ሰው ሆነህ ተነጠልህ …
ሰው ሆነህ ተመለስህ
… በ’ኛ ውስጥ ልትኖር
ኖቨምበር ፪፣ ፪፲፻፩፯
The post ኒርቫና appeared first on Bawza NewsPaper.