Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Ethiopia: Gojjam Dembecha City|ደምበጫ!

$
0
0
ደምበጫ!
ሀገሬ ልዪ ናት ፡
የበርካታ አመታት ታሪክ የሞላባት፡
ስሟ በእግዜር ታምር የተሰየመላት።
በ1771 የሚካኤልን ታቦት ጠባቂ መነኩሴ፡
ወንበዴ ቀማኛ ወጋቸው ባንካሴ፡
ተቆጣ ሚካኤል የመነኩሴውን ደም አደረገው ቢጫ፡
ካህናት ይጮሀሉ እያሉ ደም ቢጫ ደም ቢጫ፡
ከዚህም ተነስተው ስያሜዋን ሰጧት ተባለችደምበጫ
ጉላ ወንዝ ለሁለት ከተማዋን ከፍሏት ውበት ያለበሳት
ቀጨም እነ ብር ወንዝ የሚጋልቡባት
የሙላለም ችግኝ ውበት የለገሳት
አየሯ ምግብ ነው ሰቀለ ማሪያም ደን ለገፍ ነው የሰጣት
ኢትዮጵያዊ ሁሉ ባይጎበኛት እንኳን በዝና ያውቃታል
ሆድ ፈዋሽ አረቄዋን አስልኮ ቀምሶታል
ጠላዋ እንጀራ ነው ሲባል ሰምቶላታል
ማሯን አጣጥሞ የማይላት የለም ይች ሀገር ደግ ናት
እስኪ ይህን በሉኝ እምየ ደምበጫ የለም ያልተቸራት
አንዱ ባለቅኔ እንዲህ ተቀኘላት
“ከሸገር መለስ ከጎጃም ገነት
አለች አንዲት ሀገር ደምበጫ እሚሏት
ጎበዝ ጀግና ቆንጆ የሚበቅልባት
ሚካኤል በታምር የነገሰባት
የትም ወልደሽ ደምበጫ ጣይው የተባለላት”
አመሰግናለሁ እንኳን ተቀኙላት
ይች ናት ሀገሬ ክርስቲያን ሙስሊሙን በፍቅር የያዘች
ሌላ እምነት አትሻም በሯን ቆልፋለች
ሁሌም በጥር በጥር ደምበጫ ሰርጓ ነው
ሚካኤል እና ባታ እያነገሰች ነው
ጥር 12 ቀን ወጣቱን ነው ማየት
እያለ ሲያረግድ የሚካኤል ለት አለብኝ ስለት
ለታቦቴ ስገድ ለታቦቴ
ለታቦቴ ሚካኤል አባቴ
ያኔ ለወጣቱ ቃል ያጣል አንደበቴ
ብቻ ክፉ አይንካችሁ
ወጣችሁ ግቡልኝ ሁሌም አልጣችሁ
ሚካኤል ከለላ ጋሻ ይሁናችሁ
ሀገርህ ሀገርህ ለምትሉኝ ይች ናት ደምበጫ ሁሌ የምላችሁ!
ከኦላን ይዞ በማንነቱ ፍለጋ

The post Ethiopia: Gojjam Dembecha City| ደምበጫ! appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles