Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

ሎሚን በውሃ የመጠጣት ጥቅም

$
0
0

ሎሚ እንደ ካልሲየም፣ ፖታሲየም፣ ቫይታሚን ሲ እና ፔክቲን ፋይበር ያሉ ለጤና ጠቃሚ የሆኑ ማዕድናትን በውስጡ የያዘ ለጤና እጅግ ጠቃሚ የፍራፍሬ አይነት ነው።
1.ሎሚ ዋንኛ የቫይታሚን ሲ መገኛ በመሆኑ ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙ የጎለበት እንዲሆን ይረዳል፣
2. በሎሚ ውስጥ የምናገኘው ፔክቲን ፋይበር ለአከርካሪ ጤንነት ጠቃሚ ሲያደርገው፥ ሎሚ ፀረ ባክቴሪያም ነው፣
3. የሰውነታችን የፒ ኤች መጠን እንዲስተካከል ይረዳል፣
4.ለብ ያለ የሎሚ ጭማቂ በየጠዋቱ መጠጣት ጎጂ ንጥረ ነገሮችን ከሰውነታችን ለማስወገድ ያግዛል፣
5.ሎሚ የምግብ መፈጨት ሂደትን ያቀላጥፋል፣
6. ሎሚ በሲትሪክ አሲድ እና ካልሲየም፣ ፖታሲየም፣ ፎስፈረስ፣ማግኒዚየም በተሰኙ ለጤና እጅግ ጠቃሚ በሆኑ ማዕድናት የበለፀገ ነው፣
7.በሰውነታችን ኢንፌክሽን እንዲከሰት የሚያደርገውንና ፓቶጀኒክ ባክቴሪያ የተባለው የባክቴሪያ ዝርያ ዕድገትን በመግታት በሰውነታችን ጉዳት እንዳይደርስ ያደርጋል፣
8.በጉበታችን ውስጥ የሚገኘው የኦክስጅን እና ካልሲየም መጠን ያመጣጥናል፣ ለልብ ህመም አንድ ብርጭቆ የሎሚ ብርጭቆ መውሰድ ጥር የማስታገሻ ዘዴ ነው፣
9.በመገጣጠሚያ አጥንቶች ላይ የሚከሰት ህመምን ለማስታገስ ይረዳል፣
10.በሎሚ ውስጥ የምናገኘው የፖታሲየም ማዕድን የአዕምሯችንን እና የነርቭ ስራዎችን ያግዛል፣
11.ለቆዳችን ወሳኝ ሲሆን፥ የቆዳ መበለዝ፣ መቆጣት፣ መገርጣት እና ወዝ አልባ መሆንን ይከላከላል፣
12.ሎሚ የአይን ጤንነት እንዲጠበቅ እና የተሻለ እይታ እንዲኖረን ያግዛል፣
13.ለምግብ መፈጨት የሚያግዙ ኢንዛይሞችን ተግባር ያግዛል፣
14.እንደ ጉንፋን ያሉ ህመሞችን ለመፈወስ ፍቱን ነው።
ምንጭ፦ ካነበብነው

The post ሎሚን በውሃ የመጠጣት ጥቅም appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles