Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Ethiopia: Bahir Dar University | Save Tana Lake |ዩኒቨርሲቲው የእንቦጭ አረምን በስነ-ህይወታዊ ዘዴ ለማጥፋት ምርምሮችን እያካሄደ ነው

$
0
0

ዩኒቨርሲቲው የእንቦጭ አረምን በስነ-ህይወታዊ ዘዴ ለማጥፋት ምርምሮችን እያካሄደ ነው
========================
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የእንቦጭ አረም በጣና ላይ መከሰቱን የዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች ካሳወቁበት ጊዜ ጀምሮ አረሙን ለማስወገድ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ የቆየ ቢሆንም አረሙን ማስወገድ አልተቻለም። አረሙ በጣና ሀይቅና በአዋሳኙ በሚገኙ 5 ወረዳዎች ላይ ነው የተከሰተው፡፡ ችግሩ የተከሰተባቸው ሀገራት ስነ ህይወታዊ ዘዴ/ጢንዚዛ/ በመጠቀም ውጤታማ የሆነ ስራ እንደሰሩ የተለያዩ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲም የእንቦጭ አረምን በሳይንሳዊ ዘዴ ለማስወገድ 150 የሚሆኑ እንቦጭን ብቻ የሚመገቡ ጢንዚዛዎችን ከወንጅ ስኳር ኮርፖሬሽን የምርምር ማዕከል በማምጣት የተለያዩ የሙከራ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ከምርምሩ በተገኘው ውጤት መሰረት እንቦጭን ለማጥፋት ጢንዚዛዎች አይነተኛ መድሃኒት መሆናቸውን በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በብሉ ናይል ውሃ ምርምር ተቋም ተመራማሪ እንዲሁም በባዮሎጂ ት/ት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው በነበሩ ገልፀዋል፡፡ ጢንዚዛዎችን በማራባት በአሁኑ ሰዓት ቁጥራቸውን ከ2000 በላይ ማድረስ የተቻለ ሲሆን 1000 የሚሆኑትን በዚህ ወር አረሙ በተከሰተባቸው አካባቢዎች እንደሚለቀቁ ዶ/ር ጌታቸው ጨምረው ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ሰዓት ጢንዚዛዎችን በስፋት በማርባት ለማከፋፈል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
እንቦጭ አረምን ለማጥፋት ህብረተሰቡ ያለውን ተነሳሽነት እና ቁርጠኝነት እጅግ በጣም የሚደነቅ መሆኑን ዶ/ር ጌታቸው ገልፀው አረሙ ከተነቀለ በኋላ ግን መቃጠል እንዳለበት ጨምረው አሳስበዋል፡፡

Bahir Dar University, Bahir Dar, Ethiopia 

The post Ethiopia: Bahir Dar University | Save Tana Lake |ዩኒቨርሲቲው የእንቦጭ አረምን በስነ-ህይወታዊ ዘዴ ለማጥፋት ምርምሮችን እያካሄደ ነው appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles