Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Ethiopia: Gojjam!

$
0
0

ስለ ጎጃም ይህን ያውቃሉ?
ጎጃም የጤፍ፣የማርና የወተት ምድር ብቻ ሳይሆን እልፍ የጥበብ ሰወችን ያፈራ ምድር ነው፡፡
ለአብነትም፡- ☞
1,ሀዲስ አለማየሁ ✍ፍቅር-መቃብር
2,አቤ ጎበኛ ✍አልወለድም
3,ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ(የመጀሪያውን የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር የፃፉ ታላቅ ደራሲ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ )
4,በውቀቱ ሰዩም ✍ከአሜን ባሻገር
5,ጌትነት እንየው ✍ገጣሚ ከያኒ
6,አፈወርቅ ገብረ እየሱስ ✍#ጦቢያ የመጀመሪያው(የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ )ረጅም ልቦለድ ደራሲ
7,አበረ አዳሙ ✍ፍቅር በሲዖል ውስጥ
8,ሊቀ ተዋናይ (የቅኔ ፈጣሪ)
9,አባ አብርሃም (በግዕዝና በአማርኛ የመጀመሪያው መፅሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ በአፍሪካ ምድር)
10,አለቃ አያሌው ታምሩ(ሊቀ ሊቃውንት)
11,እማሆይ ገላነሽ(የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የሴት የቅኔ መምህርት)
12,አቡነ ቴዎፍሎስ(ሁለተኛው የኢትዮጵያ ፓትሪያሪክ
13,ሰገነት ቀለሙ international center for insect physiology &Ecology አለም አቀፍ ድርጅት ጄኔራል ዳይሬክተር(Pathologist)እና Loreal-uniand award ተሸላሚ በተጨማሪም Forbes መፅሔት ከ 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ የአለማችን ሴቶች ውስጥ አካቷቸዋል
14,መልዐከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ(ሊቀ ሊቃውንት እና ኢትዮጵያ የራሷ ጳጳስ እንዲኖራት ትልቅ ስራ የሰሩ)
15,ዶ/ር ኢሳይያስ አለሜ(ከመጀመሪያ የኢትዮጵያ የዶክትሬት ተመራቂወች በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀና በወቅቱ በምስራቅ አፍሪካ ታዋቂ ሌክቸረር የነበረ…)
16,ተመስገን ገብሬ ✍የጉለሌው ሰካራም(በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው አጭር ልቦለድ ፀሐፊ )
17,አምሳለ ጓአሉ(በኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያዋ ሴት ካፒቴን )
18,አያልነህ ሙላቱ(ባለቅኔ ፀሐፌ ተውኔት)
19,አለቃ ተክለ እየሱስ ዋቅጅራ፦✍የጎጃም ታሪክ፣የጎጃምን ትውልድ እና ካርታ በማዘጋጀት የደከሙ ጥበበኛ እና ታላቅ ባለቅኔ ደራሲ እና ሰዓሊ(አለቃ ተክለ እየሱስ ወለጋ ተወልደው ጎጃም ያደጉ፣የኖሩ፣ ያስተማሩ፣ለጎጃም ታላቅ ፍቅር የነበራቸው እና ከጎጃም ታላላቅ ሰዎች ውስጥ የሚመደቡ ናቸው፡፡)
20,መላኩ በጎሰው✍ነይ ነይ በደመና፣ታላቁ ዳኛ እና ብዙ ተውኔቶችን የፃፉ)
21,ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው(ታላቁ የቅኔ መምህር)
22,ዶ/ር ስዩም አየሁኔ(የ Harvard ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ሳይንቲስት(Vice President of Immunological Systems at MatTek corporation )
23,ዶ/ር እንዳወቀ ይዘንጋው(የአሜሪካ የጂኦፊዚካል ማህበር አባል እና በቦስተን ኮሌጅ ስር ባለው የሳይንሳዊ ምርምር ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ)
24,አውግቸው ተረፈ✍ወይ አዲስ አበባ፣ዕብዱ፣የፕሮፌሰሩ ልጆች እና ታላቅ ደራሲ እና ተርጓሚ…ለአብነት ያህል እንጅ ለቁጥር የሚያታክቱ ደራሲያን፣አለም አቀፍ ሳይንቲስቶች እና የአገር ባለውለታዎች እንዲሁም ለጠላት እሬት የሆኑ ጀግኖች
እንደ ፦
ደጃች ተድላ ጓሉ፣ንጉስ ተ/ሀይማኖት፣ራስ ሀይሉ፣በላይ ዘለቀ(አባ ኮስትር)፣እጅጉ ዘለቀ፣ሽፈራው፣መንገሻ ጀንበሬ፣ሀይሉ በለው፣ነጋሽ በዛብህ፣ደጃች ብሩ ጎሹ፣ራስ መርዕድ ኃይሉ… የመሳሰሉ ጀግኖች ያፈራ ውብ ምድር እና ድንቅ የአምላክ ስራ ካረፈባቸው፦
—> ጣና ሀይቅ(በኢትዮጵያ 1ኛ ከአፍሪካ 3ኛው ሀይቅ
—>ግዮን (አባይ)የአለም የመጀመሪያው ረጅሙ ወንዝ መነሻ ምንጭና የጢስ አባይ መገኛ፣(ግዮን ጎጃምን 340°(ዲግሪ)ይዞራታል፡፡ይኸውም፦”የሁለተኛው ወንዝ ስሙ ግዮን ነው፡፡ርሱም የኢትዮጵያ ምድር ሁሉ ይከብባል፡፡”(ኦሪት ዘፍጥረት 2፡13)
—>ታምራዊው የዘንገና ሀይቅ
—>ጮቄ አራት መከራከር(የምስራቅ አፍሪካ የውሃ ማማ፣
—>ባህረ ጊዎርጊስ ሀይቅ(ይህ ታምራዊ ሀይቅ ውሃው ላይ ድንጋይ ሲቀመጥ በላይ ይንሳፈፋል)…
በርካታ ጥንታዊ አብያተክርስቲያናትን የያዘ እንደ፦
ዲማ ጊዮርጊስ፣መርጦለ ማርያም፣ደብረ ወርቅ ማርያም ፣እንጦስ እየሱስ፣ዳጋ እስጢፋኖስ፣አብማ ማርያም፣ባህርዳር ጊዎርጊስ፣ዋሸራ ማርያም፣ጣባ ኖላዊ፣ደብረ ኤሊያስ …ወዘተረፈ የሞሉበት የአምላክ ድንቅ ስራ ምድር ነው፡፡
በመጨረሻም ባህላችንን እና አገራችንን የምንጠብቅበት እና የምንወድበት ልብ አምላክ ይስጠን፡፡
Tesfaye Negusse facebook page

The post Ethiopia: Gojjam! appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles