Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

የሊቃዉንት መፍለቂያ ደብረ ገነት ኤልያስ

$
0
0

የደብረ ኤልያስ ቤተክርስትያን በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ በደብረ ኤልያስ ከተማ ይገኛል፡፡ቤተ ክርስትያኑ የተመሰረተዉ በ15ኛዉ ክፍለ ዘመን በአጼ ዘርዓያዕቆብ ዘመነመንግስት በ1466 ዓ/ም ነዉ፡፡የአሁኑ ቤተክርስትያን ህንጻ የተሠራዉ ከየካቲት 15 እስከ ሀምሌ 16/1964 ዓ/ም በሁለተኛዉ የኢትዮጵያ ጳጳስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የግል ገንዘብ ነዉ፡፡ይህ ቤተ ክርስትያን በ1912 ልዑል ራስ ሃይሉ ተክለሃይማኖት በጭቃ ጡብ ያሰሩት ላይ ቤት፣መሃል ቤት እና ምድር ቤት የሚባሉ 3 ክፍሎች ያሉት እቃ ቤት አለዉ፡፡ የቤተክርስትያኑ ዉድሞ የቤተክርስትያኑ ግርማ ሞገስ ሲሆን የተመልካችን ቀልብ ይስባል፡፡የዉድሞዉ አሰራር መጀመሪያ ከ1946-1952 ዓ/ም ሲሰራ በ7 ክፈፎች በጭቃ ጡብ/የህንጻ/ ስራ ተፈጽሞ ፣በሳር ክፍክፋ ክዳን ለብሶ ነበር፡፡

ከ2 ዓመት በኋላ ግን ከ1954-1955 ዓ/ም ድረስ ክዳኑ ወደ ቆርቆሮ ግድግዳዉ ጡብ በጭቃ ተለስኗል፡፡ይኸዉ ቆርቆሮም ከድፍን 44 ዓመታት አገልግሎት በኋላ በ1999 ዓ/ም በ3500 ቆርቆሮ ተቀይሯል፡፡በደብረ ገነት ኤልያስ ቤተክርስትያን ለደብሩ አስተዳዳሪዎች የሚሰጥ የማዕረግ ስያሜ “ድምሐነ-ገነት”የሚል ሲሆን ትርጓሜዉም “የገነት መሃል ወይንም ራስ “ማለት ነዉ፡፡ይህ ስያሜ የራሱ የሆነ ትርጓሜ ሲኖሩ በሌሎች አብያተ ክርስትያናት እንደማይሰጥ አባቶች ይገልጻሉ፡፡ በዚህ ቤተክርስትያን የሚገኙ ድሮ ሰዉ የነበሩ ናቸዉ ተብለዉ በአፈታሪክ የሚታመኑ ሁለት ድንጋዮች አሉ፡፡ድንጋዮችም ሰዉ በነበሩበት ሰዓት ባልና ሚስት ሙሽሮች ሆነዉ ወደ ባልየዉ ሀገር ጉዞ ሲደረግ ሴቷ ሙሽራ ባስከተለችዉ ጥፋት የደረሰባቸዉ ቅጣት ለአሁኑ ድንጋይነታቸዉ እንዳበቃቸዉ ይነገራል፡፡ድንጋዮቹ በመጠንና ቅርጽ ፈጽሞ የተለያዩ ናቸዉ፡፡ህብረተሰቡ በተለይም በበዓል ሰዓት ሴቷን ሙሽራ ለማንሳት የተለያዩ ሙከራዎችን ያደርጋሉ፡፡ድንጋዋን በማንሳትም ህብረተሰቡ የተለያዩ አንድምታዎችን ይሰጣሉ፡፡
የደብረ ገነት ኤልያስ ቤተክርስትያን ከጥንት እስከ ዛሬ የዜማ፣ቅኔ፣አቋቋም፣መጽሐፍና የቅዳሴ መርጌታዎች መፍለቂያ ማዕከል ነዉ፡፡ከዚህ ቦታ የእዉቀት መነሻቸን አድርገዉ በዓለምና ሀገር አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ ምሁራንን ይኸዉ ቤተ ክርስትያን አፍርቷል፡፡


ከእነዚህም ጥቂቶቹ፡-
 ታላቁ ደራሲና የቤተ ክህነት ሊቅ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ
 ሁለተኛዉ ኢትዮጵያዊ ተወላጅ ጳጳስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
 የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ
 ክቡር ደራሲ መላኩ በጎሰዉ
 ታላቁና እዉቁ የረጅም ልብ ወለድ ድርሰት አባት ክቡር ዶክተር ሀዲስ አለማየሁ
 ዶክተር ኢሳያስ አለሜነህ ከብዙ በትቂቱ መጥቀስ ይቻላል፡፡አሁንም ይህ የሊቃዉንት መፍለቂያ ቦታ ስራ አልፈታም በ5ቱ ጉባኤያት በርካታ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

ምንጭ ካነበብነው

The post የሊቃዉንት መፍለቂያ ደብረ ገነት ኤልያስ appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles