Mengistu Zegeye
የወሎ ዘማቾች ተነስተዋል! !!!!!
ሆ ብየ እመጣለሁ ፤ ሆ ብየ በድል ፤
ወትሮም የአባቴ ነው ጠላትን መንቀል! !!!!!!
እንግዲህ በዚያ ሰሞን የወሎው ሎጎ ሃይቅ ለጣና በላከው የወንድም ናፍቆት ደብዳቤ ተክዘን ሳለ ፤ የኦሮሚያው ቢሾፍቱ ሃይቅ ለጣና የጦመረውን የናፍቆት ደብዳቤ አንብበን ሳንጨርስ ወይኔ ወንድሜን እያለ ሲቆጭ የከረመው ድፍን የወሎ ዘማች እነሆ ማቄን ጨርቄን ሳይል የንቀል ዘመቻውን ዳር ለማድረስ አንዲት ቀን ብቻ ቀርቶታል ። በስራ መደራረብ ምክንያት በነዚህ 3 ቀናት ወንድሞቼን በአካል ተገኝቼ ማገዝ ባልችልም ከወንድም Temesgen Tessema ጋር እያንዳንዷን እንቅስቃሴ እየተናበብን ሃሳብ እየተለዋወጥን ዘመቻው መልክ እየያዘ ነው! !! ጎበዝ! ! ዘመቻው የማንም አይደለም!!!! የሁላችንም እንጅ!!! ማንም ዘመቻውን የወደደ ይከተለን! !!! ጣናን ከእምቦጭ ልክፍት ለመታደግ ወሎየዎች እምቦጭን በዱኣና በዱላ ሊገጥሙት ተነስተዋል! !!! እናንተ የወሎ ወጣቶች እጅግ ኮራሁባችሁ! እባካችሁ !! ይህችን ግጥሜን ጀባ ልበላችሁ! !!! መርሃባ በሉኝ! !!!!
!!!!ላንቡጭለት! !!!!!!
((የወሎው ሎጎ ሃይቅ ለጣና የላከው))
እንዴምን ከርመሃል ወንድም አለም ጣና ፤
እኔስ ጠረጠርኩኝ ፤
ደህናም አልመሰልከኝ ፥
እንደው ይኸን ሰሞን ያቀባዥረኛል ሌሊቱን በጠና ።
ዛሬ አመሻሹ ላይ ደውየ ነበረ ለአቢጃታ ለጫሞ ፤
አልሰማህም እንዴ ፤
ጠበል ወስደውታል አያ ጣና ታሞ ።
ሲሉኝ ይህ ጉልበቴ በቆሞኩበት ከዳኝ ፤
ከበሽታህ ይልቅ አለመስማቴ ነው አስብሶ የጎዳኝ ።
ውሃ እየታመመ ፤
ወንዝ እያዘመመ ፤
ባህር እየከዳ ባቄመበት ሃገር ፤
ውሃ ታሟል ብሎ ማን ጃሎ ሊናገር ፤
ማን ሃኪም ሊመጣ ፤ ማን ጎበዝ ሊገደር ፤
ይኸ የወንዜ ሰው ፤
ወግ ማረግ አርጎታል ፤
ባህር እየሰጠ ፤ ለጅረት መግደርደር ።
እናም ጣና ጓዴ፤
የጎጃሙ ሰንደቅ ፤
ያባይ ባልንጀራ ፤
የዘጌ ሰገነት ፤
ታሟል ዛሬ ሲሉኝ ደግሞ ዛሬ አመመኝ ፤
ወንድሜን ሳላየው ፤
የከረመ ናፍቆት መጥቶ ገረመመኝ ።
እናምልህ ጣና ፤
በእርግጥ መታመምህ ፤ ብርቅ አይደለም ጓዴ ፤
በጦቢያ ውሃ ላይ ፤
ከታወጀ ቆየ የውሃ ዳር ውርዴ ።
ያው እንደምታውቀው ፤
የዛሬ ስንት አመት ፤
ሃረማያ ሞቶ ፤
ሬሳ ሸኝተን ቀብረን ስንመጣ ፤
አስታውሳለሁኝ ፤
ነግረኸኝ ነበረ ፤
እንዲሁ እንደሚሆን ነገ የኛም እጣ ።
ብለኸኝ ነበረ ፤
ሃበሻ ከንቱ ነው ያባት ወግ ይሽራል ፤
ባህሩን ገብሮ ጅረት ይበደራል ።
መቼም ወንድማለም ፤
የተናገርከው ቃል ዛሬም ይገርመኛል ፤
ሰሚ የለም እንጅ ፤ እኔንም አሞኛል ።
አንተ ቀድመህ ወድቀህ ህመምህ ሲነገር ፤
ማን ያይልኝ ይሆን መገን የኔን ነገር ።
ህመምክን ስሰማ ፤
እመጣለሁ ብዬ ነይቼ ነበረ ፤
ያባይ ገመገሙን ላየው ያንን መልካ ፤
ወሳንሳ ደርበህ ፤
ከመልካው ሽንጥ ላይ ተኝተሃል ለካ ።
በተግዳሮት ቅኔ፤
በሙሻዘር ኑሮ ፤
ፈተና እየበዛ ክንድ እየረገበ ፤
እዚህ የደረስነው ፤
በወጀብ መሃከል መሆኑን ብናውቅም ፤
ካባይ ዳር የቆመው ፤
የጊወን ዳር ማተብ ፤
የጎጃሜው ሰንደቅ ፤ባንዲራው አይወድቅም ።
አውቃለሁ ባያሌው ፣
የበላይ ከተማ ፣
የሽፈራው ቀዬ ፤
በበልጂግ በሞይዘር ፤
ቆራርጦ ሚጥለው ፤ ጠላቱን በሜዳ ፤
እንኳን ላገር እምቦጭ፤ አይተኛም ለባንዳ ፤
መቼስ ወንድም ታሞ ፤
መቼስ የናቴ ልጅ ፤ ከጠፋበት መላ ፤
ወንድም ለዛሬ ነው ፤
ምን ይረባል ሆታ ከሞቱ በኻላ ።
ይኸው ዛሬ ወሎ ፤
በቅዳሜ ሰማይ ፤
ዱኣየን ሳልጨርስ ጉዝጓዝ ሳይነሳ ፤
በጀማው ምንሽር ፤
ቱፍታ እየወረደ ሃገሬው ሲደሳ ፤
ጣና ከሃይቁ ዳር ፤
የበቀለው ቅጠል ፤
በአበጋሩ ጓንዴ ፤ ከስሩ ተነሳ! !!
አመመው ወንድሜን ፤
ብየ ልኬ ነበር ፤ ታቹን በቦረና ፥
ንቀል ይላል ዛሬ ፤
የአባ መንሽር ቀለም የበላይ ነውና ።
ይህንን ሲሰማ ፤
አባይ ተጨነቀ ጣናም ተጋባበት ፤
የእምቦጩ ማንቦጫ መንቀያው መጥቶበት ፤
የወሎው ሳቢሳ ፤
የወንድሜን አረም፤ ሂጄ ላንቡጭለት! !!!!
ጃኖ መንግስቱ
The post Ethiopia: Wollo for Lake Tana | የወሎ ዘማቾች ተነስተዋል! !!!!! appeared first on Bawza NewsPaper.