በዚህ ፎቶ ላይ የሚታዩት እነ ማን ናቸው? በስንት አመት ምህረት ነው ፎቶውን የተነሱት? እንዚሀ ሰዎች በጋራ አንድ ጉልህ ስህተት ፈጽመው ነበር:: ምን ነበር ያ ስህተት? በፎቶው ላይ ሁሉም አንድ የጋራ መጠሪያ ተሰቷቸው ነበር:: ይህ መጠሪያ ምን ይባላል? እጃቸውን ያነሱት ማንና ማን ናቸው? የእጃቸው አነሳሰ ላይ ምን ልዩ ነገር ይስተዋላል? መልሱ እንደሚከተለው ነው:
1.በፎቶውላይ ከፊትለፊት የሚታዩ ት ከግራ ወደ ቀኝ: የብሄራዊ አትሌቲክስ አሰልጣኝ ንጉሴ ሮባ : አትሌት ብርሃኑ ግርማ : ምሩጽ ይፍጠር: ደረጀ ነዲና መሃመድ ከድር:: ከኋላ የሚታዩት ከግራ ወደ ቀኝ: አትሌት እሸቱ ቱራ : ግርማ ወልደሃና : ቶሎሳ ቆቱ: ከበደ ባልቻ ( ተሸፍኗል)::
2: ፎቶውን የተነሱት ስፔን ሀገር የተደረገው የ1973ቱን አ.ም. ( በአውሮፓ አቆጣጠር 1981) የአለም ሃገር አቋራጭ 12 ኪሜ ውድድር ላይ ለመካፈል በሚጓዙበት ወቅት ነው::
3: የፈጸሙት ስህተት: ውድድሩን ሁሉም አንድ ላይ ሆ ነው እየመሩ ሳለ ገና ለመጨረስ 2 ዙር እየቀራቸው አንድ ዙር ብቻ የቀራቸው መስሏዋቸው በከፈተኛ ፍጥነት ሮጠው ውድድሩ ሳያልቅ መቆማቸው ነው:: ከመካከላቸው መሃመድ ከድር እንደምንም የቀረውን ዙር በስሀተታቸው ተጠቃሚ የሆ ነውን አሜሪካዊ ሯጭ (ክሬግ) ተከትሎ 2 ኛ ወጣ:: ሌሎቹ ለመጨረስ ያህል ብቻ ሮጠው ግርማ ብርሃኑ 7 ኛ: ደረጀ ነዲ13 ኛ: ከበደ ባልቻ 14 ኛ : ምሩጽ ይፍጠር 15 ኛ እሸቱ ቱራ 30ኛ : ግርማ ወልደሃና 32ኛ ቶሎሳ ቆቱ 75ኛ ሆነው ጨረሱ:፡ይህ ውጤት ደረጃቸውን አይወክልም:: በ 1979 የአለም 10000 ሜተር ሻምፒዮና ምሩጽ ክሬግን እጅግ አዋርዶት ነው ያሸነፈው ( Yifter blew craig away፣said the commentator)::
4: የጋራ መጠሪያቸው አርንጓዴው ጎርፍ ( Green flood) ይህም የሆ ነው በዚህ ውድድር ላይ ሁሉም አትሌቶች አርንጓዴ ቀለም ያለው መለያ ለብሰው ውድድሩን በከፍተኛ ፍጥነት እጅብ ብለው በጋራ በመሮ ጣቸው ነው::
5: እጃቸውን ወደ ላይ ያነሱት አትሌቶች ብርሃኑ ግርማ እና ምሩጽ ይፍጠር ናቸው:: እጃቸውን በመጨበጥ ወደ ላይ ያነሱበት ፋሽን በአጠቃላይ የተጨቆኑ ወዛደሮች የትብብርና አንድነት መፈክር ፋሽን ሲሆን ሁለቱም አትሌቶች ግራ እጃቸውን ነው ያነሱት: ይህ ደግሞ የወቅቱን ኢትዮጵያን ጨምሮ የኮምኒስትን ርእዮተ አለምን በሚከተሉ ሀገሮች የተለመደ ፋሽን ነበር::
Source: Ababu Teklemariam Tiruneh face book page
The post በዚህ ፎቶ ላይ የሚታዩት እነ ማን ናቸው? በስንት አመት ምህረት ነው ፎቶውን የተነሱት? appeared first on Bawza NewsPaper.