ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5636 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰባ ስድስት (176) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3521 ደርሷል። ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 28 (17 ከጤና ተቋም እና 11 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን አንድ ናሙና ከጤና ተቋም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። በተጨማሪ ሁለት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ (60) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡ በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰባ አምስት (75) ሰዎች (31 ከአዲስ አበባ፣ 28 ከሶማሊ ክልል፣ 10 ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአማራ ክልል እና 1 ከአፋር ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 620 ነው።Ministry of Health,Ethiopia

