ከሰሞኑ የወጣ ጥናት እንደሚያመለክተው ከሆነ በቀጣዮቹ 20 ዓመታት ለስትሮክ በሽታ የሚጋለጡ ሰዎች ቁጥር በ59 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ይችላል።
ጥናቱ ለዚህ በሽታ ምክንያት ናቸው በሚል ከሚያነሳቸው ውስጥም ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት፣ በቂ አካላዊ እንቅስቃሴ አለማድረግ እና ያልተስተካከለ የአመጋገብ ስርዓትን ይዘረዝራል።
በእንግሊዝ የስትሮክ ማህበር የተሰራው ጥናት በስትሮክ በሽታ ጥናቶች ላይ 10 ሚሊየን ዩሮ ኢንቨስት በማድረግ ብቻ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር እስከ 2035 ለስትሮክ በሽታ ሊጋለጡ የሚችሉ 114 ሺህ ሰዎችን መታደግ ይቻላል ብሏል።
ስትሮክ ምንድ ነው…?
ስትሮክ በብዛት ወደ አእምሯችን መግባት ያለበት ደም ሲቋረጥ አሊያም መጠኑ ሲቀንስ የሚከሰት የበሽታ አይነት ነው።
በጣም ከባድ ከሚባሉ በሽታዎች ውስጥ የሚካተት ሲሆን፥ በበሽታው የተጠቃውን ሰው እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላልም ተብሏል።
ለስትሮክ በሽታ የተጋለጡት እነማን ናቸው….?
የዓለም የጤና ድርጀት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015 ባወጣው ሪፖርት መሰረት ስትሮክ በዓለም ላይ በገዳይነት ከሚጠቀሱት በሽታዎች ውስጥ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ለስትሮክ በሽታ በብዛት የተጋለጡ ሰዎች በእድሜ የገፉ አሊያም አዛውቶች ናቸው የተባለ ሲሆን፥ ሆኖም ግን በማንኛውም እድሜ ላይ ሊከሰት ይችላል ተብሏል።
ህፃናትም ጭምር ለበሽታው የመጋለጥ እድል አንዳላቸው ነው የሚነገረው።
የስትሮክ ምልክቶች….?
በስትሮክ የተጠቃ ሰው ላይ በብዛት ከሚታይ ምለከት ውስጥ የፊት ጡንቻ በአንደኛው በኩል መውረድ መዛል፤ አልፎ አልፎ በአንድ በኩል ያለ አየን እና ጡንቻም ከፊት ጋር አብሮ ወደ ታች መውረድ ነው።
በተጨማሪም በንግግር ጊዜ መንተባተብ አሊያም ግልፅ አድርጎ ማውራት አለመቻል፤ አልፎ አልፎም ሙሉ በሙሉ መናገር አለመቻል ከምልክቶቹ ውስጥ ተጠቃሽ ነው።
እንዲህ አይነት ምልክቶችን እኛ ላይም ይሁን ሌሎች ሰዎች ላይ ካየን በአፋጣኝ አምቡላንስ በመጥራት በአቅራቢያችን ወደሚገኝ የጤና ተቋም መሄድ ይመከራል።
ስትሮክን ለመከላከል….?
ስትሮክን ለመከላከል ቀለል ያ የአኗኗር ዘርቤ ለውጥ ማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ይነገራል።
ከእነዚህም ወስጥ ጤና የሆነ የአመጋገብ ስርዓት መከተል እና በየእለቱ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ መልካም ነው ተብሏል።
ምንጭ፦FBC
The post የስትሮክ በሽታ ምንድን ነው፤ ምልክቶቹና መከላከያውስ appeared first on Bawza NewsPaper.