ሰበር ዜና
በቅድስት እስራኤል እየሩሳሌም የሶስት ሺህ ዘመን ታሪክ ያለው ቅርሳችን በተደጋጋሚ ባለቤት በማጣቱ በዛሬው እለት አርብ ተደርምሷል የሚባል ዘገባዎች እየሰማሁ ነው እጅጉን በማዘንና እንባ በማንባት ቁጭቴን እየተወጣሁ ነው ይህ ቅርስ ክርስቲያን አይሁድ እስላም የማይል ሁላችንንም የሚያስተኛ የሆነ ትልቅ መለያቸው ነው (ኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ውርስና ቅርስ) የሚባል በሰሜን አሜሪካ መቀመጫውን ያደረገ ብዙን ግዜ በውስጥ መስመር በዚህ ጉዳይ ላይ ፅፌ ነበር ዙሪያውን የግሪክ የአርሜንያ የግብፅ የራሻ መንግስታት የተቀደሰውን ቦታቸውን አስከብረው ሲያሳድሱ የኛ ብቻ ባለቤት እንደሌለው ብቻውን እራቁቱን ሆኖ መቅረቱ እጅግ ያማል አልፎ ተርፎ ካድሬ ቄሶች መጫወቻቸው አድርገውት አባቶቻችንን ጠባቂዎቻችንን ለጠገበ አረብ እያስመቱ ይገኛሉ በተለይ በሰሜን አሜሪካ በየ አመቱ ደስ የሚል ፕሮግራም የውርስና ቅርስ የሚል ጀረባታችሁ ደቅናችሁ አሸብርቃችሁ ብር የምትሰበስቡ በሙሉ ልታስቡበት እራሳችሁን ልትገመግሙበት አስቸኳይ በመሆኑ ልታስቡበትና የእስራኤል መንግስትን የፉጥኝ ይዛችሁ ይህን የተከበረ ቦታ አሳድሶ ለወደፊት ትውልድ ማስተላለፍ የናተ የኛ የሁላችንም ሐላፊነት ነው ይህ ቦታ እንደ ነብሰ በላ ዙሪያውን ከበው ያሉት ቦርቡረው ቦርቡረው እረቁቱን አስቀርተው ይኸው ዛሬ ከባድ ዜና እየሰማን ነው በድሮ መንግስታት ባልወለድም ለዚህ ታሪካዊ ቦታ ጀግኖቻችንን ትልቅ እርብርብ እንደሚያደርጉ እንደነበር ታሪክ ሰምቻለሁ ስለዚህ መላው ክርስቲያን አይሁድ እስላም ሳይባል ለዚህ ቅርሳችን ቦታ ልንነሳ ይገባል ብዙን ግዜ ኢሳትም ይሁን ተዋቂ ሰዎች ይህን ቦታ ትኩረት እንዲሰጡበት መልክት ተላልፎ ነበር እባካችሁ ለዚህ ቦታ እንድረስለት መንግስት አልባ የሆነችው ሃገራችን ጭንቋ በዝቷል ቅርሳችን ሳይቀድም እንነሳ ወያኔያውያን ምቀኞች በተደጋጋሚ እስራኤል የሚመጡት ቦታውን ለማስደፈር እንጂ ተገቢ የሆነ ከእስራኤል መንግስት ጋር ተነጋግረው ይህን ቦታ ለማሳደስና ለማስከበር ሳይሆን ለማስደፈር ነው የሚመጡት ደፍረውም ከነ ጫማቸው ገብተው አሳይተዋል ሌላው ጋር ግን በክብር ነበር የገቡት ኢትዮጵያ አልጠፋ ታሪኳ አልጠፋ ሁለመናዋ አልላቀቅ ብሏቸዋል አፈራርሰው እሳት ጭረው ለኳኩሰው ነው የመሄድ ጥረታቸው ይሄን በሀገርም የምንመለከተው ነው በውጭም እንደዛው ስለዚህ በአለም ላይ ያለነው በሙሉ እየሩሳሌም ላሉት አብያተ ክርተስቲያን በየ ቤተ ክርስቲያኑ የምንጥለው ገንዘብ ትልቅ ነው የጥንታዊን ቦታ ከእስራኤል ባለ ስልጣናት ጋር ተነጋግሮ የማስከበሩ ሁኔታ ሐላፊነት አለብን ስለዚህ እያንዳንዳችን እንነሳ ።
The post ሰበር ዜና ! በቅድስት እስራኤል እየሩሳሌም የሶስት ሺህ ዘመን ታሪክ ያለው ቅርሳችን በተደጋጋሚ ባለቤት በማጣቱ በዛሬው እለት አርብ ተደርምሷል……..! appeared first on Bawza NewsPaper.