በኢትዮጵያ የሥነ ፅሁፍ ታሪክ ለረጅም ዓመታት በሐያሲነት የሰራው አብደላ እዝራ በትላንትናው ዕለት በ58 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ በዛሬይቱ ኢትዮጵያና በአዲስ ዘመን ጋዜጦች እንዲሁም የደራሲያን ማሕበር በሚያሳትመው ብሌን መፅሔት ላይ ለበርካታ ዓመታት የሒስ ስራዎቹን አቅርቧል፡፡ ከታላላቅ ቀደምት የኢትዮጵያ ፀሐፍት እስከዛሬ ወጣት ደራሲያን ድረስ የአብደላ የሂስ ብዕር የኢትዮጵያን ሥነ ፅሁፍ በጥልቀት ቃኝቷል፣ ተችቷል፣ አቅጣጫ ጠቁሟል፡፡ ከዛሬ 2 ዓመታት ጀምሮ ደግሞ አብደላ እዝራ የሒስ ስራዎቹን በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በተከታታይ ለአንብብያን እያቀረበ ነበር፡፡ አብደላ እዝራ የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበር፡፡ ሐያሲ በአብደላ እዝራ ሞት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽ፤ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለአድናቂዎቹና በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሁፍ ወዳጆች መጽናናትን እንመኛለን፡፡
↧