Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

በጎፋ ጋዜ ማስቃላ ናፍቆት-ከአልባ ዙማ እስከ ጋልማ

$
0
0

በጎፋ ጋዜ ማስቃላ ናፍቆት-ከአልባ ዙማ እስከ ጋልማ | ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም መስቀልን መናፈቅ በሚል የመስቀልን ድባብ እየተረከልን ነው፡፡ ከዳሞታ ተራራ ግርጌ ከወላይታዎች ጊፋታ የጀመረው ትረካ ዛሬ ወደ ጎፋዎች መንደር ገብቷል፡፡ የጎፋ ጋዜ ማስቃላን ገጽታዎች እንዲህ ይተርክልናል፡፡ | ሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

አልባ ትልቁ ተራራ፣ የካዎቹ ሞገስ ዘመናት ሲሻገር የተመለከተው ባለ እድሜ፤ አሁን የጎፋዎችን መንደር ናፍቆኛል፡፡ ልቤ ማዜ ወንዝ እስኪጎድል ጠብቆ ለመሻገር ትእግስት የለውም፡፡ የውርጭ ተራሮች በልምላሜ በሚያሸበርቁበት በዚህ ወቅት ሳውላ መሆን መታደል ነው፡፡ በዚህ ወቅት ብልቂ መግባት መባረክ ነው፡፡

ከጎፋ ጋር አብሮ ዮ! እንደማለት የዘመን አጋጣሚ የለም፡፡ እዚህ ከሁሉ የሚበልጠው ቀን ማስቃላ ነው፡፡ ዱዛ የሰው ቀልብ የሚስብበት የልምላሜው ወቅት ነው፡፡ የዛላ ዛዬ ሹቻ ናፍቆት ያላዩት ሀገር የሚለውን ይቃረናል፡፡

ያላ ሳውላ የትም ያለን በትዝታ የምትጎትት ከተማ ናት፡፡ የሆሴ ዜማ ጆሮን ሰላሳ ጊዜ ቢያራግፉት ደጋግሞ ማቃጨሉን አያቆምም፡፡ የጋሼ ባህላዊ ጨዋታ ኦ ሆያ ጋሼ ከአብሮነት ትዕይንቱ ጋር ከዓይን ላይ ሳይጠፋ ስለሚኖርበት ምድር ሳስብ ማስቃላን እናፍቃለሁ፡፡

ጎፋ ጋዜ ማስቃላ አይሰለችም፡፡ ዘለዓለም አብሮ የሚኖር ትዝታ ነው፡፡ የጎፋዎች ምርቃት ማስቃላን ዘለዓለም ከመኖር ጋር ይተሳሰራል፡፡

ምኞታቸው በበረከት የተሞላ ነው፡፡ አህያ ቀንድ እስክታበቅል፣ ልጃገረዶች አግብተው እስኪያልቁ፣ ያ ተራራ የኖረውን ዘመን በመኖር መስቀልን ለማየት የሚመኝ ባህል ውስጥ መኖር ጸጋ ነው፡፡

አንድ ቀን በኢትዮጵያ ትልቁ ኩነት ጎፋ ጋዜ ማስቃላ እንደሚሆን አምናለሁ፡፡ ያኔ ሩቅ የለም፡፡ ለጋዜ ማስቃላ የመጣ ጎብኚ በዎምባ ፏፏቴ ይጠበላል፡፡ የሊዲ ፏፏቴ ውበት የካሜራ ብርሃኖች ያብረቀርቁበታል፡፡

READ  ብሔራዊ ጥቅም የማስጠበቅና ገፅታ የመገንባት ስራ የዲፕሎማት ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዜጋ ሊከናወን ይገባል ተባለ

ግንድ አንሳን የሚሳለም፣ ጋልጣ ማርያም ደጃፍ እልል የሚል ብዙ ነው፡፡ በመሎኮዛ ቅመም ያበዱ ምግቦችን እየተመገበ የሀገሬ ሰው መስከረምን እንደ አደይ ጎፋ ላይ ያብባል፡፡ ጎፋ ጋዜ ማስቃላ ይናፍቃል፡፡

ከተራሮች አናት እስከ ማዜ በርሃ መንፈሱ ሁሉ አንድ ነው፡፡

በቶ፣ ጋልማ፣ ቡልቂ፣ ላሃ…..የትም ይሁን ብቻ ማስቃላን አብሮ መሆን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ከዚያ ማስቃላ ገባ ተብሎ ወጣ የለም፡፡
ጎፋ በጊያ ካንሶ አድምቆ ይሸኘዋል፡፡

ማስቃላን ለማሰናበት ባህላዊ ክንዋኔው ሲደምቅ ደቦጭ በና ሆኖ አብሮ በጊያ ካንሶ ትዕይንት በደስታ እንደማበድ መልካም እድል የለም፡፡ የመስቀል ናፍቆት ሩቅ ተጓዥ ነው፡፡

ከደቡብ ስሜን የሚወረውር፣ የጨዋ ሰፈር ደመራን ከገነት ተራራ ስር ከጎንደር ልጆች ጋር እንለኩሳለን፡፡ ኢዮሃ መስከረም፡፡

SOURCE:DIRETUBE

The post በጎፋ ጋዜ ማስቃላ ናፍቆት-ከአልባ ዙማ እስከ ጋልማ appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles