Quantcast
Channel: Bawza
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

ከዚህ በኋላ ያገኙትን የሞባይል ቀፎ ገዝቶ በኢትዮጵያ ኔትወርክ ውስጥ መጠቀም ስለማይቻል ቀፎ ሲገዙ እንዳይከስሩ ይህችን ምክር ይተግብሩ፦

$
0
0

(Tsegaw Melaku)
· 
፠••••••••ከዚህ በኋላ ያገኙትን የሞባይል ቀፎ ገዝቶ በኢትዮጵያ ኔትወርክ ውስጥ መጠቀም ስለማይቻል ቀፎ ሲገዙ እንዳይከስሩ ይህችን ምክር ይተግብሩ፦
አንድ ሞባይል ቀፎ ሲመረት ለራሱ መለያ ብቻ ሆኖ የሚያገለግል ባለ 15 ዲጂት ቁጥር አለው። 
ይህ መለያ ቁጥር IMEI ኮድ በመባል ይታወቃል። 
አንድ ሰው *#06#ን ሞባይሉ ውስጥ በማስገባት ሲደውል፤ይህንን የIMEI ቁጥር ያገኛል። 
ሆኖም አንዳንድ ተመሳስለው የተሰሩ ፎርጅድ የሞባይል ቀፎዎች የሌሎችን መለያ ቁጥር የሚይዙበት ሁኔታ ስላለ ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የሞባይል ቀፎዎች ተመሳሳይ IMEI ኮድ ሊኖራቸው ይችላል።
ኢትዮ ቴሌኮም እንደዚህ አይነቶቹን የሞባይል ቀፎዎች በራሱ ኔትወርክ አማካኝነት የለየ መሆናቸውን አስታዉቋል። ቁጥራቸውም 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን አካባቢ ነው። 
እነዚህን የሞባይል ቀፎዎች የያዙ ሰዎች በኢትዮቴሌኮም ኔትወርክ እንዲገለገሉ የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ አንድ አመት ብቻ ነው።
ከአንድ አመት በኋላ እነዚህ የሞባይል ቀፎዎች ሙሉ በሙሉ በኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ውስጥ እንዳይሰሩ ይደረጋል።
በመሆኑም ገንዘበዎ በከንቱ እንዳይጠፋ ከዚህ በኋላ የሞባይል ቀፎ ሲገዙ የሞባይል ቀፎው በኢትዮጵያ ኔትወርክ ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን እርግጠኛ መሆን መቻል አለበዎት። 
ይህንንም ለማረጋገጥ የሚጠቀሟቸው የሚከተሉት ዘዴዎች አሉ፦
1- የሚገዙት ሞባይል ቀፎ ውስጥ ሲም ካርድ ማስገባት 
2-*868# ላይ መደወል(በዚህ ወቅት ሶስት አማራጮች ይመጣሉ። 
እነዚህም አማራጮች 
1-Phone Unlock
2-Switch Lock
3-Check Status) የሚሉ ናቸው። ከሶስቱ አመራጮች ሶስተኛውን(Check Status) ለመምረጥ በሚመጣው ክፍት ቦታ 3 ቁጥርን አስገብቶ Send የሚለዉን መጫን በዚህ ወቅት ሁለት አማራጮች ይመጣሉ እነዚህም አማራጮች ፤
1 By IMEI 
2 By Phone number የሚሉ ናቸው።
ከዚያ By IMEI የሚለዉን ለመምረጥ በተሰጠው ክፍት ቦታ ላይ 1 ቁጥርን ያስገቡ። ከዚያም ሴንድን(SEND) እንደተጫኑ Enter IMEI number የሚል መጠይቅ ይመጣለዎታል።
በዚህ ወቅት ሊገዙት ያሰቡትን ሞባይል ቀፎ መለያ ቁጥር በዚህ ክፍት ቦታ ውስጥ በመፃፍ sendን ይጫኑ። ወዲያዉኑ በኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ውስጥ የሚሰራ ቀፎ መሆኑ አለመሆኑን ያረጋግጣሉ።
አለበለዚያ ከዚህ በኋላ ካርቶኑ ያልተፈታና በዚህ መልኩ ያልተሞከረ ሞባይል ገዝተው ገንዘበዎን ሊቀልጡ ይችላሉ። 
በተለይ የታሸገ ሞባይል ቤተዎ ወስደው « ለሶስት ሰአታት ያህል ቻርጅ ያድርጉ» በሚል ኮዱን ሳይሞክሩ ቤተዎ የሚወስዱ ከሆነ ፤ በመጨረሻ ቻርጅ አድርገው ሲሞክሩት IMEI ኮዱ ከኢትዮቴሌኮም ኔትወርክ ጋር የማይጣጣም ከሆነ ተሸወ ዱ ማለት ነው። 
፠፠፠ በነገራችን ላይ እነዚህን ምክሮች አሁን፠፠፠
በያዙት ሞባይል ቀፎ መምከር ይችላሉ።
•••••• ይህችን ምክር ለሌሎችም ያጋሩ።፠፠፠፠
አመሰግናለሁ

source: EthioVoice.net

The post ከዚህ በኋላ ያገኙትን የሞባይል ቀፎ ገዝቶ በኢትዮጵያ ኔትወርክ ውስጥ መጠቀም ስለማይቻል ቀፎ ሲገዙ እንዳይከስሩ ይህችን ምክር ይተግብሩ፦ appeared first on Bawza NewsPaper.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1835

Trending Articles