‹‹ እኔ የመጣሁት የአማራ እና የኦሮሞን ህዝብ ተፈጥሯዊ ትስስር ለማጠናከር ነው፡፡ ››
‹‹ኦሮሞ እና አማራ ለኢትዮጵያ ትልልቅ መሰረቶች ናቸው።›› ጃዋር ሙሃመድ
ባሕር ዳር፡ነሀሴ 03/2010 ዓ.ም(አብመድ) የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ ጃዋር ሙሀመድ እና ሌሎች አክቲቪስቶች ባሕር ዳር ገቡ፡፡
በባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ የአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በአቀባበሉ የተገኙት የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ.ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ‹‹ኦኤምኤን በአማራ ክልል ያለውን ልማትና ዴሞክራሲ ለማስፈንና ለውጡን ለማጠናከር አጋር ነው፤ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እና ከክልሉ ህዝብ ጋርም በጋራ ይሰራል›› ብለዋል፡፡
ጃዋር ሙሀመድ በአቀባበል ስነ-ሰርዓቱ እንደተናገረው በአሁኑ ወቅት ላለው ለውጥ የአማራ ህዝብና መንግስት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ‹‹የአማራ እና የኦሮሞን ህዝብ ተፈጥሯዊ ትስስር ለማጠናከር ነው የመጣሁት›› ነው ያለው አቶ ጃዋር፡፡ ‹‹የሁለቱን ህዝቦች ትስስር ለማጠናከር የምችለውን አደርጋለሁም›› ብሏል፡፡
አቶ ጃዋር ሙሀመድ ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዘጋቢ፡- ግርማ ተጫነ
Source:Amhara Mass Media Agency
The post የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ ጃዋር ሙሀመድ እና ሌሎች አክቲቪስቶች ባሕር ዳር ገቡ appeared first on Bawza NewsPaper.