ፈረንሳይ ቡሩንዲ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በኩል ለአቅመ ደካሞች ያቀረበችው የአህያ ስጦታ ፕሮጄክት ቁጣን ቀስቅሷል።
ከታንዛኒያ የተገዙት አህዮቹ በቡሩንዲ ገጠራማ አካባቢ የሚገኙ ሴቶች እና ህጻናት የግብርና ምርቶችን ወደ ገበያ እንዲወስዱበት እንዲሁም ውሃ እና ማገዶን እንዲያመላልሱ ታስቦ ነበር ለአካባቢው ነዋሪዎች የተበረከቱት።
ሆኖም ግን የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት አማካሪ የፈረንሳይ ግብረ ሰናይ ድርጅት አህያን ገዝቶ የማከፋፈል ፕሮጀክት “ሀገሪቱን እንደመስደብ የሚቆጠር ነው” ብለዋል።
የሀገሪቱ የግብርና ሚኒስትር ዴኦ ጉይዴ በበኩላቸው የቡሩንዲ ገጠራማ አካባቢአስተዳዳሪዎች አህዮቹን በአፋጣኝ እንዲሰበስቡ የጠየቁ ሲሆን፥ አህዮቹ ከሀገር የሚወጡበት መንገድ በፍጠንት እንዲመቻችም አሳስበዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ፥ አህዮቹ ወደ ቡሩንዲ የገቡት አስፈላጊውን ሂደት ሳያልፉ ነው።
ፕሮጀክቱ በይፋ በተመረቀበት ወቅት ተገኝተው የነበሩት በቡሩንዲ የፈረንሳይ አምባሳደር ላውረንት ባደረጉት ንግግር፥ የእንስሳት ላንድ ክሩዘር የሆኑትን አህዮች ወደ ቡሩንዲ ማምጣት መልካም ስራ ነው ሲሉ አወድሰው ነበር።
አህዮቹ ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡም አስፈላጊውን ሂደት ማለፋቸውን ነው አምባሳደሩ ያስታወቁት።
መቀመጫቸውን ቡሩንዲ ያደረጉ አንድ የአውሮፓ ዲፕሎማት እንደሚናገሩት ከሆነ፥ ፈረንሳይ የሩንዲ ፕሬዚዳንት የስልጣን ቆይታ ማራዘሚያ ህገ መንግስት ማሻሻያ ህዝበ ውሳኔን በመተቸቷ ነው ቡሩንዲ ይህንን የምታደርገው።
ዲፕሎማቱ ለዚህ በማሳያነትን ሩዪጊ በተባለው ግዛት በቤልጂየም መንግስት ድጋፍ ተመሳሳይ ፕሮጄክት ተከናውኖ ከቡሩንዲ መንግስት ምንም አይነት ተቃውሞ አለመነሳቱን ያነሳሉ።
The post France’s ‘Donkey Diplomacy’ Backfires In Burundi appeared first on Bawza NewsPaper.