የዕለቱ ቢያንስ አንድ እንቁላል መመገብ በልብ ህመም የመያዝ እድልን እንደሚቀንስ ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡ ተመራማሪዎቹ ጥናቱን ያካሄዱት 416 ሺህ በሚደርሱ አዋቂ ቻይናውያን ላይ ሲሆን ከዚህ ቀደም ካንሰርና መሰል በሽታዎች ያልተጠቁ መሆናቸው ፡፡
እንቁላል በባህሪው ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን ይዘት ያለው ሲሆን ከዚህ ቀደም የህክምና ባለሙያዎች ለሰዎች ብዙ እንቁላል እንዳይመገቡ ይመክሩ ነበር፡፡
ሆኖም በየዕለቱ እንቁላል የሚመገቡት ከማይመገቡት ይልቅ በ18 መቶ በህመሙ የመያዝ እድላቸውን ቀንሷል፡፡
በተጨማሪም በጥናቱ እንቁላል ተመጋቢዎች ከማይመገቡት ይልቅ በ26 በመቶ በስትሮክ የመያዝ እድል መቀነሱንም ገልጸዋል፡፡
ለዘጠኝ ዓመታት በዘለቀ በዚህ ጥናት 9 ሺህ 985 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ እንዲሁም 5 ሺህ 103 የሚደርሱት ከልብ ህመም ጋር በተገናኙ በሽታዎች ተጠቅተዋል፡፡
በቻይና ከልብ ህመም ጋር የተገናኙ በሽታዎች ቁጥር አንድ ገዳይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
Source: CNN and FBC
The post An egg a day might reduce your risk of heart disease, study says appeared first on Bawza NewsPaper.